Amharic

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች

መመርመር ለምን ያስፈልግዎታል

መመርመር ህይወትን ያድናል። ምርመራ ሰዎች የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት፣ በጊዜው እንደ ማቆያ ያሉ ጥንቃቄዎችን እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል፤ የበሽታው ምልክት የሌላቸው ሰዎች አሁንም ቫይረሱን ሊያስተላልፉ ይችላሉ። እንዲሁም መመርመር የህዝብ ጤና ባለስልጣናት ወረርሽኙን ለይተው እንዲያውቁ፣ እና አዳዲስ የቫይረሱ ተለዋጮችን ለመከታተል ይረዳል። መመርመር መደበኛ እንቅስቃሴዎችን ለመቀጠል የሚረዳ አስፈላጊ አካል ነው።

የ University of Washington ተመራማሪዎች እና የጤና ጥበቃ ክፍል Department of Health (DOH፣ የጤና መምሪያ) የ COVID-19 ምርመራ እና በ WA Notify (የዋሺንግተን ማሳወቂያ) የሚደረግ ክትትል ከዲሴምበር 2020 እስከ ማርች 2021 ድረስ ወደ 6,000 የሚጠጉ ኬዞችን ለመከላከል እንዳስቻለ ደርሰውበታል።

መቼ መመርመር አለብዎት

የ COVID-19 ምልክቶች ካለብዎ ወይም ለ COVID-19 ፖዘቲቭ ከሆነ ሰው ጋር የቅርብ ግንኙነት ከነበርዎት ምርመራ ለማግኘት ይጣሩ። የበሽታ ምልክቶች ከታዩዎት፣ ወይም ተጋላጭነትዎን ከጠረጠሩ በኋላ በ 3-5 ቀናት ውስጥ፣ ምንም እንኳ ምንም ምልክቶች ባይታዩብዎትም ወዲያውኑ ምርመራ ማድረግ አለብዎት።

የት መመርመር ይችላሉ

የዋሽንግተን ስቴት Department of Health ድህረ ገጽ በእያንዳንዱ ካውንቲ የሚገኝ ከስራ ሰአታት እና መስፈርቶች ጋር የመርመሪያ ጣቢያዎች መዝገብ (በእንግሊዘኛ) ይይዛል። ለምርመራ ጣቢያዎች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ወደ 2-1-1 ይደውሉ። እንዲሁም ለቤት ውስጥ ምርመራ፣ የመደብር የምርመራ መሳሪያዎች እና በፋርማሲዎች የተመቻቹ፣ በቤት ውስጥ ለማዘዝ የሚገኙ ናቸው።

በእኔ አቅራብያ የምርመራ ቦታ ፈልግ (በእንግሊዝኛ)

የምርመራ ዓይነቶች

አሁን ላይ የሚገኙት ምርመራዎች ፈጣን የአንቲጂን ምርመራዎችን፣ ሞለኪውላዊ ምርመራዎችን (ሁለቱም በቤተ-ሙከራ ላይ የተመሰረቱ እና የእንክብካቤ ነጥቦች)፣ እና አንዳንድ የቤት የራስ-ምርመራን ያካትታሉ። ልዩ የሆነ የማንኛውም ምርመራ አቅርቦት እንደ ፍላጎት እና የአምራች አቅም ይለያያል።

ወጪ

በካውንቲ ወይም በስቴት በሚደገፉ የምርመራ ጣቢያዎች ለሚደረጉ ምርመራዎች ከኪስ የሚወጣ ወጪ የለም። ብዙ ምርመራዎች፣ በተለይም ምልክቶች ለሚያጋጥሟቸው ሰዎች፣ ወደ ዋስትና ሊከፈሉ ወይም በ Department of Health ድጎማ ሊደረጉ ይችላሉ። ለአገልግሎት ክፍያ የሚያስከፍሉ የምርመራ ጣቢያዎች በማውጫው ውስጥ ተገልጸዋል። አብዛኛው የጉዞ ምርመራ በዋስትና ወይም በመንግስት በሚደገፉ መርሃ-ግብሮች አይሸፈንም።

ምርመራ እንዴት እንደሚሰራ

አብዛኛው ምርመራ የሚደረገው በአፍንጫ በሚገባ ጥጥ በመጠቀም ነው። አንዳንድ ምርመራዎች ምራቅን በመሰብሰብ ሊደረጉ ይችላሉ። ተጨማሪ ዝርዝሮችን ምርመራ ላይ በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች ገጽ ላይ ማግኘት ይችላሉ።

ቀጣይ-ክትትል

ምልክቶች ካልዎት በቻሉት መጠን ቤት ይቆዩ። ፖዘቲቭ የምርመራ ውጤት ካልዎት፣ ራስዎን ያግልሉ (በ DOH/Centers for Disease Control & Prevention (CDC፣ የበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማዕከላት) መመሪያዎች መሰረት) እና በ Care Connect.] በኩል እርዳታ ይፈልጉ።